አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክት ÷ ለኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች ቤተሰቦች እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል፡፡
ሶማሊያ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን በጽናት እንደምትቆምም አረጋግጠዋል።

