Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ኅብረት የቅድመ ምርጫ ግምገማ ልዑካን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ኅብረት የቅድመ ምርጫ ግምገማ ልዑካን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት የአፍሪካ ኀብረት ለመጪው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ ምርጫ ግምገማ ልዑክ መሰየሙን አድንቀው፥ ልዑኩ ለሚያከናውናቸው ስራዎች ውጤታማነት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የቀድሞ የናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የልዑካን ቡድኑ መሪ ጂኦፍሪ ኦንዬማ በበኩላቸው፥ ልዑኩ ከመጪው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት ጋር በተገናኘ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ያለመ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

Exit mobile version