Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካ ዋንጫን ከሴኔጋል የነጠቀው አወዛጋቢው የካፍ ውሳኔ…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከወራት በፊት ሴኔጋል አሸንፋው የነበረውን የአፍሪካ ዋንጫ ለሞሮኮ እንዲመለስ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በቅርቡ በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር በተደረገው 2025 የቶታል ኢነርጂ የአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ሴኔጋል ሞሮኮን አሸንፋ ዋንጫውን ማንሳቷ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ በፍጻሜው ጨዋታ በተፈጠረው ውዝግብ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን የዳኛውን ውሳኔ በመቃወም ሜዳውን ጥለው በመውጣታቸው ጨዋታው ለደቂቃዎች ተቋርጦ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ከተቋረጠበት በቀጠለው የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታም ሴኔጋል 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆኗ አይዘነጋም፡፡

ይህን ተከትሎም የሞሮኮ እግር ኳስ ፌደሬሽን የተፈጠረውን ውዝግብ መነሻ በማድረግ ለካፍ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ቅሬታ አስገብቶ ነበር፡፡

ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴም የደረሰበትን ውሳኔ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ቦርዱ በአፍሪካ ዋንጫ ደንብ ቁጥር አንቀጽ 84 መሰረት በሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ተሸናፊ ሆኖ እንዲመዘገብ ወስኗል።

Exit mobile version