Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት፡-

(260316) -- TEHRAN, March 16, 2026 (Xinhua) -- People clear the debris among destroyed buildings at a residential area in Tehran, Iran, March 15, 2026. (Xinhua/Shadati)

👉ኢራን ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣኗ አሊ ላሪጃኒ በጥቃቱ መሞቱን አረጋግጣለች፡፡

👉የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሆ ከመከላከያ እና ከደህንነት አመራሮቻቸው ጋር የታዩ ሲሆን፣ አልሞትኩም አለሁ፤ የጠላቶቻችንን መሪዎች አንድ በአንድ እየቀጠፍን ነው፤ ወታደራዊ የበላይነትም አለን የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

👉ኢራን በበኩሏ በምታስተላልፋቸው መልዕክቶች ጦርነቱ ሜዳ ላይ የተለየ እንደሆነ እና ሚዲያ ላይ እንደሚባለው እንዳልሆነ ትናገራለች፡፡

👉በየቀኑም ስጋት አለብኝ በምትላቸው የጎረቤት ሀገራት ጭምር ሚሳዔል ትተኩሳለች፤ ድሮኖችን አሰማርተው ጥቃት ትፈጽማለች፡፡

👉የአሜሪካ አየር ኃይል የኢራን ሚሳዔል የሚገኙባቸውን የሆርሙዝ አካባቢዎች ደብድበዋል፡፡

👉በእስራኤል ራማት ጋን አካባቢ ከኢራን በተተኮሰ ሚሳኤል ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

👉የዩክሬይኑ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ እንዳሉት በኢራን ጦርነት ለመሳተፍ 201 የዩክሬን ባለሙያዎች ወደ መካከለኛው ምስራቅ አምርተዋል፡፡

👉በኩዌት በደረሰ የድሮን ጥቃት ሁለት የህክምና ባለሙያዎች በፍርስራሽ ጉዳት ደርሶባዋል፡፡

👉የኢራቁ የኩርድ ክልል እጥረትን ለመፍታት በእሱ የማስተላለፊያው ቧንባ ነዳጅ እንዲያልፍ ፈቅጃለሁ ብሏል፡፡

👉የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ አብዛኛዎቹ የአሜሪካ አጋሮች በኢራን በሚደረግ ወታደራዊ ዘመቻ መሳተፍ አይፈልጉም ብለዋል፡፡

Exit mobile version