አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ ምሽግ ደርማሽ ቦምብ ጥቅም ላይ ማዋል እንደጀመረች እየተዘገበ ነው።
2 ሺህ 270 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ቦምቡ ከመሬት በታች በተገነቡ ጠንካራ ምሽጎች ውስጥ ያሉ ዒላማዎችን በጥልቀት በመግባት የማውደም አቅም እንዳለው ተገልጿል።
የአሜሪካ ጦር በኢራን የባሕር ዳርቻ አካባቢ ባሉ የሚሳዔል ማስወንጨፊያዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ያስታወቀ ቢሆንም የትኛውን ዓይነት ቦምብ ጥቅም ላይ እንደዋለ በዝርዝር አለመግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል።
19ኛ ቀኑን በያዘው ጦርነት አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ያልተቋረጠ የሚሳዔል እና የአየር ድብደባዎችን እየፈጸሙ ናቸው።
በጦርነቱ ኢራንም ያልተቋረጠ የአጸፋ ጥቃት በእስራኤል እና በአሜሪካ አጋሮች ላይ በመፈጸም ላይ ትገኛለች።

