Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 1447ኛውን የዒድ አልፈጥር ረመዳን በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሚከናወነው የዒድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ አለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ፡፡

የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን በማወቅ ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

👉ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች (ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች በተመሣሣይ ከቦሌ በአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ለሚሄዱ አትላስ መብራት እና ፒኮኪ መብራት ላይ፣

👉ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ ለሚሔዱ አሽከርካሪዎች (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)

👉ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ለውስጥ ወደ ጋዜቦ አደባባይ ለሚመጡ (ጋዜቦ አደባባይ ላይ)

👉ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ ሳንጆሴፍ መብራት ለሚመጡ ለከባድ ተሽከርካሪዎች (አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ) ሲሆን ለሌሎች ተሽከርካሪዎች (ጥላሁን አደባባይ ላይ)

👉ከቡልጋሪያ መብራት ወደ ገነት ሆቴል ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች (ቡልጋሪያ መብራት ላይ)

👉ከልደታ ፀበል ውስጥ ለውስጥ ወደ አሹ ስጋ ቤት የሚያስወጣው (ልደታ ፀበል ላይ)

👉ከጦር ኃይሎች በከፍተኛ ፍ/ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሔዱ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ላይ)

👉ከአብነት አካባቢ በፈረሰኛ ፖሊስ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ መብራት (ፈረሰኛ ፖሊስ ካምፕ መብራት ላይ)

👉ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር መውረጃ (ሞላ ማሩ መታጠፊያ ላይ)

👉ከበርበሬ በረንዳ ወደ ድሮ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች (ቃና ዘገሊላ ዳቦ ቤት መስቀለኛ ላይ)

👉ከመርካቶ አካባቢ በተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ጥቁር አንበሳ ለሚሄዱ (ተክለ ሃይማኖት አደባባይ ላይ)

👉ከቴዎድሮስ አደባባይ በቸርችል ወደ አገር አስተዳድር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ)

👉ከ4 ኪሎ አደባባይ ወደ ውጭ ጉዳይ ለሚሄዱ (4 ኪሎ አደባባይ ላይ)

👉ከሲግናል አካባቢ በሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች (ሴቶች አደባባይ ላይ)

በበዓሉ ዕለት ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ የሚሆኑ ሲሆን÷ ከበዓሉ ዋዜማ ምሽቱ ጀምሮ በተጠቀሱት መንገዶች ላይ ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት አቁሞ መሄድ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አስገንዝቧል።

ሕብረተሰቡ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ማንኛውም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም ጥሪ አቅርቧል።

Exit mobile version