አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ ጋር በጋራ የኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ ግዙፉን የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክትን በገንዘብ መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተከረ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል፡፡
የኤግዚም ባንክ አባላትን ያካተተው የአምባሳደር ቼን ሃይ ልዑክ እና የኢትዮጵያ ልዑክ በቡድን 20 ጥላ ስር ኢትዮጵያ የዕዳ ሽግሽግ ዙሪያም መምከራቸው ተመላክቷል።
አቶ አህመድ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ የዕዳ ሽግሽግ ሂደት ቻይና ላደረገችው ገንቢ ትብብር ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በተጨማሪም ቻይና በሁሉን አቀፍ የኢትዮጵያ እድገት ለምታደርገው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

