አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡
የዒድ አልፈጥር በዓል በመላው ኢትዮጵያ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
በዓሉ በተለያዩ ከተሞች በድምቀት መከበር የጀመረ ሲሆን÷ ሕዝበ ሙስሊሙ በማክበሪያ ሥፍራዎች በመገኘት የዒድ ሶላት ሥነ-ሥርዓት እያካሄደ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በረመዳን ጾም ወቅት የነበረው የመረዳዳት እና መተሳሰብ እሴት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝቧል።
ሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና በመጠየቅ ሊሆን እንደሚገባም ገልጿል፡፡

