Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአገልግሎት ሲጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በቦሌ እና በየካ ክፍለ ከተሞች ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 19 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በቦሌ እና በየካ ክፍለ ከተሞች ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ።

ምክትል ከንቲባው በክፍለ ከተሞቹ ተገኝተው የአገልግሎት አሰጣጡን የተመለከቱ ሲሆን ÷በቦሌ ክፍለ ከተማ በነበራቸው ቆይታ በ2012 በጀት አመት የተከናወኑ ተግባራት ተብራርቶላቸዋል።

በዚሁ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደርን ጨምሮ አገልግሎት በሚበዛባቸው ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተመልክተዋል።

አቶ ጃንጥራር በክፍለ ከተማው አንድ ወረዳም ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ጎብኝተዋል።

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በተመሳሳይ በየካ ክፍለ ከተማም ድንገተኛ ጉብኝት አድርገዋል።

በዚህም ከመሬትና የተሽከርካሪ አሽከርካሪ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ያለውን ስራ ተመልክተዋል።

ይህ ጉብኝት ከትናንትናው የምክትል ከንቲባዋ ጉብኝት የቀጠለ ሲሆን÷ ያለውን ሁኔታ ለማየት እንዲሁም መስተካከል ያለባቸውን ለመለየት ያለመ መሆኑን አቶ ጃንጥራር አባይ ተናግረዋል።

በሁለቱ ቀን ምልከታዎች በተለይ አንዳንድ ወረዳዎች ላይ የአደረጃጀት ፣ የመዋቅር ችግሮች መኖራቸውን ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ክፍተት መኖሩን ታዝበናል ያሉት ምክትል ከንቲባው እነዚህን ለመፍታት ይሰራል ብለዋል።

ጉብኝቱ በቀጣይም በሌሎች ክፍለ ከተሞች የሚቀጥል መሆኑ ተጠቁሟል።

በሃይማኖት ኢያሱ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version