አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል የዒድ ሶላት በከተማችን ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መረጃ፤ መርሐ ግብሩ በስኬት እንዲከናወን ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በዚህም የሃይማኖት አባቶች፣ የፀጥታ አካላት፣ ህዝበ ሙስሊሙ እና አጠቃላይ የከተማዋ ነዋሪዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

