Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዒድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክቶ ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ 1 ሺህ 447ኛውን የዒድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክቶ ማዕድ አጋርተዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በከተማችን በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ 28ቱም የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት አቅመ ደካሞችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አረጋውያንና ለከፋ ማህበራዊ ችግር ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖቻችንን ማዕድ የማቋደስ መርሃ ግብር ተከናውኗል ብለዋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኘው 6ኛው እና በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በሚገኘው 21ኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በመገኘት ማዕድ ያቋደሱት ከንቲባዋ፤ ማዕከላቱ በዐቢይ ጾም እና በረመዳን ወቅትም ጭምር ለጾመኞች እንደየ እምነታቸዉ የአፍጥር እና የፆም ምገባ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል ሲሉ ገልጸዋል።

በማዕከላቱ ወገኖችን እየመገቡ ለሚገኙ ባለሀብቶች፣ አጋሮች እና አስተባባሪዎች በተጠቃሚዎቹ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

Exit mobile version