Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ደብረብርሃን እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል።
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ19ኛ ዙር በተለያዩ ዘርፎች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሶስተኛ ዲግሪ በመደበኛ፣ በማታ፣ በክረምት እና በርቀት መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 8 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
በዚህም 919 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 87 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ሁለት ተማሪዎች በሶስተኛ ዲግሪ ተመርቀዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር) በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ተማሪዎች በቂ ክህሎት እንዲያገኙ ዩኒቨርሲቲው በተግባር የተደገፈ ስልጠናን ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር በማድረግ እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።
ተመራቂዎች ስራ ፈጣሪ ለመሆን መትጋትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ላይ ቀዳሚ ተሳታፊ እንዲሆኑም አሳስበዋል።
በተመሳሳይ መቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ለስድስተኛ ዙር ባካሄደው የምረቃ ሥነ ሥርዓት በመጀመሪያ ዲግሪ ያስተማራቸውን 319 ተማሪዎችን አስመርቋል።
ዩኒቨርስቲው ለመጀመሪያ ጊዜ 38 ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን አሰልጥኖ አስመርቋል።
በሰላማዊት ሙሉነህ እና በአማረ ደገፋው
Exit mobile version