Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጤና ሚኒስቴር በጋሞ ዞን ለተጎዱ ዜጎች የ36 ሚሊየን ብር የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጤና ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ዜጎች 36 ሚሊየን ብር የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ለጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምስ አድማሱ (ዶ/ር) አስረክበዋል፡፡

ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት÷ አደጋው መከሰቱን ተከትሎ የሕክምና ቡድን አባላትን ወደ ሥፍራው በመላክ የሕክምና አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ደምስ አድማሱ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷የጤና ሚኒስቴር አደጋው ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ላደረገው የተቀናጀ ድጋፍ ማመስገናቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

Exit mobile version