Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሴቶች በጥበብ ይኖራሉ፤ በራስ መተማመን ይሠራሉ፤ ይችላሉም – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ማለዳ 16 ሺህ ሴቶች የተሳተፉበትን የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አስጀምረዋል፡፡
ከንቲባዋ በዚህ ወቅት÷ሴቶች በጥበብ ይኖራሉ፤ በራስ መተማመን ይሠራሉ፤ በራስ መተማመን ይሮጣሉ፤ ይችላሉም ብለዋል፡፡
ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ውድድሩ በኮሪደር ልማቱ አማካኝነት እጅግ ውብ፣ ምቹና ለከተማዋ አዲስ ዘመናዊ መልክ ባላበሰው በቦሌ – አትላስ – ኡራኤል መንገድ ላይ በልዩ ድምቀት መከናወኑን አመልክተዋል፡፡
Exit mobile version