አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ኒዮርክ ከተማ ላጋርዲያ አውሮፕላን ማረፊያ በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው ተሰምቷል፡፡
የከተማዋን ፖሊስ ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው÷ ባለቤትነቱ የኤር ካናዳና ሲአርጄ 900 የሚል ሞዴል ያለው አውሮፕላን ከሞንትሪያል ተነስቶ ላጋርዲያ አውሮፕላን ማረፊያ እያረፈ በነበረበት ወቅት ከተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ አደጋ አጋጥሞታል፡፡
በአውሮፕላኑ 76 ሰዎች ተሳፍረው የነበረ ሲሆን÷ በአደጋው ዋናና ረዳት አብራሪዎች ሕይወት ሲያልፍ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው ተመላክቷል፡፡
የአደጋው ምክንያት እስከሚጣራና የተፈጠረው ችግር እስከሚስተካከል አየር መንገዱ በጊዜያዊነት የተዘጋ ሲሆን÷ በረራዎችም መቋረጣቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡
በሚኪያስ አየለ

