አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ 81 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ሆነዋል አሉ።
ሚኒስትሩ ውሃና ስርዓተ ፆታ በሚል መሪ ሀሳብ በተከበረው የውሃ ቀን ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ ተደራሽ ካደረገችው ንፁህ ውሀ ውስጥ 50 ከመቶ ተጠቃሚዎች ሴቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዓለም ከውሃ ጋር በተያያዙ ችግሮች እየተፈተነች መሆኑን ገልጸው፥ በዚህ ችግር የሴቶች ተጋላጭነት ከፍ ያለ በመሆኑ ይህንን ለመቅረፍ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ኢትዮጵያ እየተገበረች በምትገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሴቶችን በተለያዩ መንገዶች ተሳታፊ እያደረገች እንደሆነ አንስተዋል።
በፍቅርተ ከበደ

