Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሲዳማ ክልል የአምራች ዘርፉን ውጤታማነት ይበልጥ ለማሳደግ…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል የአምራች ዘርፉን ውጤታማነት ይበልጥ ለማጠናከር በቅንጅት እየተሰራ ነው አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ “ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” ኤግዚቢሽን እና ባዛርን በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ አስጀምረዋል፡፡

አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ አምራች ዘርፉ በክልሉ ሁሉን አቀፍ ሽግግር ላይ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ይበልጥ ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው፡፡

በክልሉ ለኢንቨስትመንት ያለውን ምቹ ሁኔታ በአግባቡ በመጠቀም በተከናወነ ሥራ አበረታች ውጤት መመዝገቡን አመልክተዋል፡፡

በዚህም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ቁጥር መጨመር እንደተቻለ ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡

በክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን እና ባዛር ለተከታታይ አምስት ቀናት እንደሚቆይ ተመላክቷል፡፡

በነገዎ ብዙነህ

Exit mobile version