Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምርጥ 10 የአረንጓዴ ትራንስፖርት አማራጮችና የኢትዮጵያ ተሞክሮ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአቅርቦት ሰንሰለት ላይ ትኩረቱን ያደረገው ሰስተነብሊቲ ዲጂታል የመረጃ አውታር ሀገራት ተግባራዊ ቢያደርጓቸው ያላቸውን ምርጥ 10 የአረንጓዴ ትራንስፖርት ተሞክሮዎች ይፋ አድርጓል፡፡

ተሞክሮዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡-

  1. የኤሌክትሪክ መኪኖችን በብዛት መጠቀም
  2. ዘመናዊ የትራፊክ ማኔጅመንትና የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አገልግሎት
  3. ዘመናዊ የከተማ ፕላን እና አስተዳደር
  4. ለጭነት ትራንስፖርት የካርቦን ብክለትን የሚቀንስ ነዳጅ መጠቀም
  5. ቀልጣፋ ሎጅስቲክስ
  6. ሃይድሮጅን ነዳጅን መጠቀም
  7. ባዮፊዩል ወይም ከተክሎች፣ አልጌና ቆሻሻ የሚመነጩ ታዳሽ ፈሳሽ ጋዞችን መጠቀም
  8. የህዝብ ትራንስፖርትን መጠቀም
  9. ሰው ሠራሽ ነዳጆችን መጠቀም
  10. የብስክሌት መሰረተ ልማቶችን መገንባትና ብስክሌት መንዳትን ባህል ማድረግ

በኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ ተጽዕኖዎችን ለመቀነስና ለመከላከል  ከአየር ንብረት ጋር ተስማሚ የሆኑ የትራንስፖርት ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግ መንግስት የተለያዩ ኢኒሼቲቮች ቀርጾ ወደ ስራ አስገብቷል፡፡

ለአብነትም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መንግሥት የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን አቅርቦትና ስርጭት ለመጨመርና መሠረት ለመጣል ጉልህ የፖሊሲ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ ማበረታቻን ጨምሮ በዘርፉ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት የኤሌክትሪክና ታዳሽ ኃይል ተሽከርካሪ ተጠቃሚዎችን ፍላጎት ለማነቃቃት እገዛ አድርጓል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ተጋላጭነት ለመውጣት የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭን ጨምሮ የታዳሽ ኃይልና አረንጓዴ ኢኮኖሚን በማስፋፋት በኩል ውጤታማ የአረንጓዴ ልማት ርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች፡፡

መዲናዋን ጨምሮ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች በኮሪደር ልማት የተገነቡ የአረንጓዴ መዝናኛ ስፋራዎች  እንዲሁም የሳይክልና የእግረኛ መንግዶች የዚሁ የአረንጓዴ ትራንስፖርትና አረንጓዴ ልማት አካል ናቸው፡፡

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version