Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአማራ ክልል በርካታ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ሰላምና መረጋጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመምጣቱ በአሁኑ ወቅት በርካታ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ናቸው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰሞኑን በአማራ ክልል ባሕር ዳር እና ጎንደር ከተማ አስተዳደሮች ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ÷ የክልሉ የሰላም ሁኔታ በመሻሻሉ በአሁኑ ወቅት በርካታ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በጎንደር እና ባሕር ዳር ከተሞች በኮሪደር ልማት የተሰራው ስራም አበረታች ውጤት የተገኘበት መሆኑን ጠቅሰዋል።

የአርሶ አደሩን ኑሮ ዘመናዊ ለማድረግ አስቻይ የሆነውን የገጠር ኮሪደር ልማት መጎብኘታቸውን ገልጸው÷ በጎንደር የገጠር ኮሪደር ሞዴል መንደር መጠናቀቁን አንስተዋል።

እንዲሁም የመገጭ ግድብ በ2001 የተጀመረ መሆኑንና ረጅም ጊዜ መፍጀቱን በማስታወስ መንግስት እንደ አዲስ ብዙ ነገሮችን አስተካክሎ በትኩረት በመስራት በቅርብ ወራት እንዲጠናቀቅ ለማድረግ የሚያስችል ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ተመልክተናል ብለዋል።

ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ የመሰረተ ልማት ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር ተጨማሪ ገቢን የሚያስገኙ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

በሶስና አለማየሁ

Exit mobile version