አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀረሪ ክልል መንግስት በክልሉ በየዓመቱ ለሚከበረው የሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
የክልሉ መንግስት በመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክቱ፥ በዓሉ የክልሉን ህዝቦች የመቻቻል፣ የአብሮነትና የሰላም እሴት በማጉላትና የቱሪዝም ዘርፉን በማጎልበት ረገድ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጿል።
በዓሉ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን እንዲሁም የክልሉን ልማትና ዕድገት የበለጠ ማጠናከር በሚያስችል መልኩ በደማቅ ዝግጅት እንደሚከበር አስታውቋል፡፡
የዘንድሮውን የሸዋሊድ በዓል በተሳካ መልኩ ለማክበር የተለያዩ ኮሜቴዎች ተዋቅረው ዝግጅት ሲደረግ የቆየ ሲሆን፥ የሐረርን ታሪክ፣ እሴትና ባህል የሚያስተዋውቁ ሁነቶች ለታዳሚዎች እንደሚቀርቡ ነው የተገለጸው፡፡
የክልሉ መንግስት ባስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በዓሉ አብሮነት፣ ፍቅር፣ ሰላምና ወንድማማችነት የሚጠናከርበት እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

