Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በእንግሊዝ የሚገኙ ቅርሶችን ለማስመለስ ጥረት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን በእንግሊዝ የሚገኙ 26 ቅርሶችን ለማስመለስ ጥረት እየተደረገ ነው አለ።

ከመቅደላ ተዘርፈው ወደ እንግሊዝ ተወስደው ከነበሩ ቅርሶች መካከል አንዱ የሆነው የእቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ ወለባ (የፀጉር ጌጥ) ከ157 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል፡፡

የወለባው (የፀጉር ጌጥ) የርክክብ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ድርጅት እና በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን መካከል ተካሂዷል፡፡

በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው÷ የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለቤት የእቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ ወለባ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል ብለዋል፡፡

እስካሁን 72 ቅርሶች በሰብዓዊነት፣ በክርክርና ድርድር መመለሳቸውን ገልጸው÷ በቀጣይ በእንግሊዝ አልበርት እና ቪክቶሪያ የሚገኙ 26 ቅርሶችን ለማስመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከ150 ዓመታት በፊት የተዘረፈው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ከ7 ዓመታት በፊት ወደ ሀገር ቤት መመለሱን ይታወሳል።

በርክክብ መርሐ ግብሩ ላይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ እና ልዑል ኤርሚያስ ኃይለሥላሴን ጨምሮ የንጉሥ አጼ ኃይለሥላሴ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

በዐምደወርቅ ሽባባው

Exit mobile version