አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 23ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድርና 19ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል በዛሬው ዕለት በሐረር ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በውድድርና ፌስቲቫሉ መክፈቻ ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ መኪዩ መሀመድ፣ የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ህይወት መሀመድን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የባህል ስፖርቶች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል ላይ ከ1ሺህ 500 በላይ ስፖርተኞች ይሳተፋሉ፡፡
ውድድሩ ከዛሬ ጀምሮ በ11 የስፖርት አይነቶች ለአንድ ሳምንት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

