አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ከአሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር ጋር መለያየቱን አስታውቋል፡፡
ከሊጉ የመውረድ ስጋት ያለበት ቶተንሃም ቶማስ ፍራንክን በማሰናበት የኢጎር ቱዶርን ቅጥር መፈጸሙ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ የ47 ዓመቱ አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር ባስመዘገበው ደካማ ውጤት ከ44 ቀናት ቆይታ በኋላ ከክለቡ ጋር
ተለያይቷል፡፡
ቶተንሃም ሆትስፐር ከአሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር ጋር በስምምነት እንደተለያየ መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

