Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ያንዣበበው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስጋት…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በሚካሄደው የ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስጋት ሊኖር ይችላል አለ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል “ሰብዓዊነት ማሸነፍ አለበት” በሚል ይፋ ባደረገው ሪፖርት÷ በ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር የሰብዓዊ መብት ስጋት ሊኖር እንደሚችል አስጠንቅቋል።

በተለይም አብዛኛዎቹን መርሐ ግብሮች በምታስተናግደው አሜሪካ ሃሳብን በነጻነት ከመግለጽ እና ከኢሚግሬሽን ሕግ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ስጋቶች መኖራቸውን በሪፖርቱ አመልክቷል።

ከሀገሪቱ ኢሚግሬሽንና የጉምሩክ አስፈጻሚ (አይ ሲ ኢ) ጋር በተያያዘ ያለው ከሀገር የማባረርና የዘፈቀደ እስር በውድድሩ ላይ ያንዣበበ ስጋት መሆኑን አስገንዝቧል፡፡

በአንጻሩ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የ2026 ዓለም ዋንጫን በታቀደው መሠረት ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በስኬት ለማከናወን ዝግጅት መደረጉን አረጋግጧል፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ግን በዓለም ዋንጫ ውድድር ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

ስለሆነም ፊፋ እና የውድድሩ አስተናጋጅ ሀገራት ደጋፊዎች፣ ተጫዋቾች እና ጋዜጠኞች በውድድሩ ወቅት ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ነው ያሳሰበው፡፡

Exit mobile version