Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሁሉን አካታች የፖለቲካ ሥርዓት ተግባራዊነት…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዓመታት የለውጡ መንግሥት በኢትዮጵያ ሁሉን አካታች የፖለቲካ ሥርዓትን ተግባራዊ በማድረግ የዜጎችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ እያረጋገጠ ይገኛል።

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የማሕበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር መሐመድ አህመድ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት÷ ከለውጡ በፊት በገዥው ፓርቲ ውስጥ የነበረው የዋናና አጋር ድርጅቶች የፖለቲካ መስመር ለዜጎች ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንቅፋት ነበር።

ይህም የሀገር ሀብትን በተቀናጀ መልኩ ለመጠቀም እንቅፋት ከመሆን በላይ በፖለቲካ ተሳትፎ ላይ ለተወሰኑት ብቻ ሥልጣንን የሰጠ እንደነበር አውስተዋል።

አሁን ላይ በለውጡ መንግሥት የተተገበረው የፖለቲካ አካሄድ ሀገር ለሁሉም እኩል መሆኗን ያረጋገጠ ነው ብለዋል።

በተለይም ለዳር ሀገር ሰዎች ብርቅ የነበሩ የልማት እና መሰረተ ልማት ሥራዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ እንዳስቻለ ጠቁመዋል፡፡

በሰለሞን ይታየው

Exit mobile version