Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የትምህርት ተደራሽነትን ለማሳደግ…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግስት የትምህርት ተደራሽነትን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት “ለሀገር ግንባታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተሳትፎ” በሚል መሪ ሀሳብ በጅማ ከተማ ውይይት እያካሄዱ ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ እንዳሉት÷ የትምህርት ዘርፍን የሚያደናቅፉ ጉዳዮችን በመለየት መልካም ልምዶችን ማጠናከር ይገባል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የጋራ ማንነትን በመገንባት፣ ብሔራዊ ጥቅምን በማረጋገጥ እና እውቀትን በማፍለቅ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ አንስተዋል፡፡

ምሁራን ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት፣ የዴሞክራሲ ባህልን በማዳበር እና ሰላምን ዘላቂ በማድረግ የበለጸገች ሀገርን ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡

መንግስት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በመገንባት የትምህርት ተደራሽነትን ለማሳደግ እየሰራ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡

በመድረኩ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች፣ የትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በሲፈን መኮንን

Exit mobile version