Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቤት አቅርቦት ፍላጎትን በዘላቂነት ለመመለስ በትኩረት ይሰራል – ረሻድ ከማል (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቀጣዮቹ ጊዜያት የቤት አቅርቦት ፍላጎትን በዘላቂነት ለመመለስ በትኩረት ይሰራል አሉ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር)።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ምስረታ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ላለፉት ሶስት ቀናት “በአዲስ ምዕራፍ ለተሻለ ነገ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን÷ በዛሬው ዕለት የበዓሉ የማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል።

ረሻድ ከማል (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ የበዓሉ ዓላማ በባለፉት ዓመታት የተገኙ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እና ከክፍተቶችም ትምህርት ለመውሰድ ነው።

ተቋሙ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ስኬታማ ጉዞ ማድረጉን ገልጸው÷ በኮርፖሬሽኑ የተከናወነው የሪፎርም ስራ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል።

ተቋሙ ባለፉት 50 ዓመታት በርካታ ውጣ ውረዶችን እንዲያልፍና አሁን ላለበት ስኬት የላቀ አስተዋጽኦ የነበራቸውን አካላት አመስግነዋል።

በቀጣይም በርካታ ስራዎች በእቅድ መያዛቸውን ገልጸው÷ የቤት አቅርቦት ፍላጎትን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ኮርፖሬሽኑ ለሰው ልጅ መሰረታዊ በሆነው የቤት ፍላጎት ላይ እንደሚሰራና ባለድርሻ አካላትም ከተቋሙ ጋር በቅርበት እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ ህንጻዎች ያስመረቀ ሲሆን÷ ሀገራዊ ለውጡን መነሻ አድርጎ በተቋማዊ ሪፎርሙ የተመዘገበውን ስኬት የሚያስቃኝ ዐውደ ርዕይም ለዕይታ ክፍት ሆኖ ቆይቷል።

Exit mobile version