አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የዋልያዎቹን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ቸርነት ጉግሳ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በድምር ውጤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን 4 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ድልድል ላይ መካተት ችላለች፡፡

