Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

 የቻይና ባንክ ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎቱን አሳየ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይና ባንክ ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ማስፈፀሚያ የሚውል የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎቱን አሳይቷል፡፡

የቻይና ባንክ ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎቱን አሳየ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይና ባንክ ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ማስፈፀሚያ የሚውል የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎቱን አሳይቷል፡፡

ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተወጣጣ የኢትዮጵያ ልዑክ ከቻይና ባንክ አመራሮች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱ ወቅት የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የቴክኒካል ዲዛይን፣ የፕሮጀክቱን ማጠናቀቂያ የጊዜ ሰሌዳ እና የሚያስፈልገውን ፋይናንስ በተመለከተ ለቻይና ባንክ አመራሮች ገለጻ ተደርጓል፡፡

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የበረራ ማዕከልነት ከማሳደግ በተጨማሪ እንደ ንግድና ቱሪዝም ያሉ ዘርፎችን በማጠናከር ለኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ልዑክ አብራርቷል፡፡

የቻይና ባንክ አመራሮች በበኩላቸው÷ ባንኩ በአፍሪካ በሚገኙ የአየር መንገድ ፕሮጀክቶች ላይ ኢንቨሰት የማድረግ ልምድ እንዳለው በመግለጽ÷ ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ባንኩ በአፍሪካ ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ የሚያስችለውን የፋይናንስ ማዕቀፍ ለመገንዘብና የትብብር መስኮችን ለመዳሰስ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በውይይቱ ሁለቱ ወገኖች በቴክኒካል እና በፋይናንስ ድጋፍ ዘርፍ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version