Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በፍቼ ከተማ በሀገራዊ ለውጡ ለመጣው ስኬት እውቅና የሚሰጥ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት አስመልክቶ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማ በለውጡ ለተገኘው ድልና ስኬት እውቅና የሚሰጥ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ባስተላለፉት መልዕክት ከመጋቢት እስከ መጋቢት በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸው፤ በመጋቢት 24 ተምሳሌታዊ ጉዞ እና መሰረታዊ ርምጃ የተመዘገቡ ስኬቶችን አድንቀዋል።

በለውጡ መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትን በመደገፍ፣ በቀጣይም የተሻለ ስራ እንዲሰራ ከመንግሥት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ የሚያረጋግጡ መልዕክትም አስተላልፈዋል።

በዚህም በመጋቢት 24 ፍሬ ወደ ተምሳሌታዊ ጉዞ፣ መጋቢት 24 ጠንካራ መሰረት የተምሳሌትነት ጉዞ ስንቅ፣ መሰረት ባለው ርምጃ ወደ ተምሳሌትነት፣ መጋቢት 24 የተምሳሌታዊነታችን መሰረትና መፍለቂያ ነው፣ የመጋቢት 24 ፍሬዎች የተምሳሌትነት ጉዞ የትውልድ ብልፅግና ነው የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

በተጨማሪም መጋቢት 24 የኢትዮጵያ ለውጥ መነሻና ብልፅግና መሠረት ነው፣ መጋቢት 24 በመስዋዕትነት መጣ በመስዋዕትነት እንጠብቀዋለን የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

በፈጠነ ዘውዴ

Exit mobile version