Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምክር ቤቱ የወንጀል ሕግ ሥነ ስርዓትና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የወንጀል ሕግ ሥነ ስርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል፡፡
ረቂቅ ሕጉ በወንጀል ፍርድ ሂደት የተጠርጣሪንና የተከሳሽን እንዲሁም በወንጀል ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ሰብአዊ መብቶች ለማስከበር የአሰራር ስርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
የተቀላጠፈ የፍትህ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል ልዩ የወንጀል ምርመራ ዘዴ እና ለተጎጂዎች ካሣ የሚከፈልበትን አግባብ ያካተተ ዓለም አቀፍ መርህን የተከተለ ረቂቅ ሕግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም በህገ መንግስቱ፣ በወንጀል ሕጉ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ህጎች የተረጋገጠና ልዩ ትኩረት የሚያሻቸው ሴቶች፣ ህፃናትና አካል ጉዳተኞች የተሰጣቸውን መብቶች የተከተለ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ ረጅም ጊዜ የቆየና የዘገየ ቢሆንም በህዝቡ ዘንድ የቅሬታ ምንጭ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ ሥነ ስርአት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 በመሆን በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል፡፡
Exit mobile version