Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢንዱስትሪን ከተገነጠለ ደሴትነት ወደ ዘላቂ ሥነ ምኅዳር…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ በሚገኙ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ከ200 በላይ ባለሀብቶች እየተሳተፉ ነው አለ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፡፡
ጽ/ቤቱ ያለፉትን ስምንት የለውጥ ዓመታት ጉዞ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ እና የወጪ ንግድ አቅጣጫ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡
የኢንዱስትሪ ንድፉ አምራች ኢንዱስትሪውን፣ ሎጂስቲክስ እና አገልግሎቶችን ወደሚያቀናጁ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚያስገኙትን ጠቀሜታ ለማረጋገጥ ትኩረት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
የኢንዱስትሪ ፖሊሲ እና የወጪ ንግድ አቅጣጫ ከሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችና ሌሎች አምራች ዘርፎች ጋር የኢኮኖሚ ትሥሥር እንዲጠናከር ማድረጉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገልጿል፡፡
በዚህም በ2010 ዓ.ም በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች 36 ኩባንያዎች የነበሩ ሲሆን፥ አሁን ላይ ከ200 በላይ ባለሀብቶች በልዩ ቀጣናው እየተሳተፉ ነው፡፡
የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ድርሻ ወደ 65 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን፥ ይህ ሽግግር ኢንዱስትሪን ከተገነጠለ ደሴትነት ወደ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ሥነ ምኅዳር መለወጡን የሚያሳይ ነው፡፡
ከልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ለወጪ ንግድ የሚቀርበው ምርት በየጊዜው እያደገ ከመምጣቱ በተጨማሪ በተኪ ምርቶች ላይ ጥገኛ የሆነውን ከአምራች ዘርፎች የወጪ ንግድ አማራጭ እያሰፋ ይገኛል።
Exit mobile version