አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋና ላምሮት ምዕራፍ 22 የድምጻዊያን ውድድር በነገው ዕለት ቀጥሎ ይካሄዳል።
በውድድሩ በዚህ ሳምንት የምድብ አንድ ሰባት ተወዳዳሪዎች ከዛየን ባንድ ጋር ሥራዎቻቸውን በሁለት ዙር ያቀርባሉ።
ለ13 ሳምንታት በሚዘልቀው በዚህ ምዕራፍ ተወዳዳሪዎች በተለያዩ ሳምንታት በራሳቸው፣ በዳኞች እና በተመልካቾች የሙዚቃ ምርጫ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።
በምዕራፉ ለፍጻሜ ለሚደርሱ አራት ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት የተዘጋጀላቸው ሲሆን÷ ለፋና ላምሮት 6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ያልፋሉ።
ነገ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥን፣ በፋና+፣ በፋና ፌስቡክ፣ በፋና ዩቲዩብ እና ቴሌግራም ገጾች እንዲሁም በ www.fanamc.com በቀጥታ ይከታተሉ።
ፋና ላምሮት ከ2011 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ የበርካታ ባለተሰጥኦ ድምጻውያን መፍለቂያ በመሆን ለሀገራዊ የኪነ ጥበብ ዕድገት አሻራውን እያኖረ ይገኛል።

