አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት አጀንዳቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክበዋል፡፡
መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም የተጀመረው የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት አጀንዳ የማሰባሰብ ሒደት በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡
የትግራይ ክልል የባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ በሦስት ቡድኖች ተከፋፍሎ ሲከናወን እንደነበር ተመላክቷል፡፡
በዛሬው ዕለት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማኅበራትና ተቋማት እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች በንዑሳን ቡድኖች ተከፋፍለው አጀንዳዎቻቸውን በቡድን ውይይት አጠናክረው አስረክበዋል።
በቡድን ውይይት የተጠናከሩ አጀንዳዎች ለጠቅላላ የትግራይ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ቀርበው ሐሳብና አስተያየት ተካትቶባቸው የሚጸድቁ ይሆናል።
በዓለምሰገድ አሳዬ

