አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኤፍ ኤ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ከሊቨርፑል ዛሬ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ ከካራባኦ ዋንጫ ድል መልስ የኤፍ ኤ ዋንጫን ለመድገም እና የውድድር ዓመቱን ለማሳመር ይጫወታል፡፡
ቀያዮቹ በበኩላቸው ÷ የዋንጫ ተስፋቸውን እውን ለማድረግ የሞት ሽረት ትግል የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
ተጠባቂው ጫዋታ በዛሬው ዕለት ቀን 8 ሰዓት ከ45 ሲል በኢቲሃድ ስታዲየም ጅማሮውን ያደርጋል፡፡
በሌሎች የውድድሩ ጨዋታዎች ቼልሲ ከፖርትቬል ምሽት 1 ሰዓት ከ15 እንዲሁም አርሰናል ከሳውዝ ሃምፕተን ምሽት 4 ሰዓት ይጫወታሉ፡፡
በቼልሲ በኩል አርጄንቲናዊው ኮከብ ኤንዞ ፈርናንዴዝ በሥነ ምግባር ቅጣት የዛሬውን ጨዋታ ጨምሮ በሊጉ ክለቡ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ እንደሚያልፈው አሰልጣኝ ሊያም ሮሳኒየር ተናግረዋል፡፡
መድፈኞቹ የማርቲን ኦዲጋርድ እና ቲምበር አገልግሎትን በዛሬው ጨዋታ የሚያገኙ ሲሆን÷ ፔሮ ሂናካፔና መዱኬን ጨምሮ ኤብሪቼ ኤዜን በጨዋታው በጉዳት መጠቀም እንደማይችሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ጠቁመዋል፡፡
በአቤል ነዋይ

