Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ ሰማዕታት ሐውልት አካሂዷል።

የፓርቲው ሊቀመንበር አብርሃም ጌጡ በዚህ ወቅት ፥ ፓርቲው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚያደርገው ተሳትፎ በይፋ ቅስቀሳ ማድረግ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡

የምርጫ ቅስቀሳ ሒደቱ አስቻይ ሁኔታዎች ባሉባቸው አካባቢዎች እንደሚከናወን ነው የገለጹት፡፡

ዜጎች በቀሪ የመራጮች ምዝገባ ቀናት የምርጫ ካርድ በመውሰድ መሳተፍ እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ፓርቲውን በመወከል የሚወዳደሩ እጩዎች እና አባላት ተገኝተዋል።

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ ለምርጫው ያዘጋጀውን የምርጫ ማኒፌስቶ መጋቢት19 ቀን 2018 ዓ.ም ማስተዋወቁ ይታወሳል።

በሰለሞን በየነ

Exit mobile version