Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 40 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከ40 ነጥብ 37 ሚሊየን በላይ ደርሷል አለ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም፡፡

የፕሮግራሙ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሳሚናስ ሰይፉ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ መሠረት ነው፡፡

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ሒደት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተዋል፡፡

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በተለያዩ ዘርፎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ እስካሁን ከ40 ነጥብ 37 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች የዲጂታል መታወቂያ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡

የፋይዳ መታወቂያ በተለይም በፋይናንስ ዘርፉ ላይ ማጭበርበርን ከመከላከል ባለፈ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለመተግበር ከፍተኛ ሚና እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ዜጎች የባንክና የቴሌብር ሒሳብ ቁጥራቸውን ቀነ ገደቡ ሳይጠናቀቅ ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር እንዲያስተሳስሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version