አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኤፍ ኤ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ሊቨርፑልን 4 ለ 0 አሸንፏል።
በአሰልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮላ የሚመሩት የካራባኦ ዋንጫ አሸናፊዎቹ በሜዳቸውና በደጋፊያቸው ፊት ባደረጉት ጨዋታ ነው ሊቨርፑልን ያሸነፉት።
በጨዋታው የማንቼስተር ሲቲ የፊት መስመር አጥቂ ኧርሊንግ ሃላንድ በጨዋታ (2) እንዲሁም በፍጹም ቅጣት ምት (1) ግቦችን በማስቆጠር ሃትሪክ ሰርቷል።
እንዲሁም ሌላኛዋን የማንቼስተር ሲቲ ግብ ሴሚኒዮ ከመረብ ጋር ሲያገናኝ ሊቨርፑሎች በጨዋታው ያገኙትን ፍጹም ቅጣት ምት ሞሀመድ ሳላህ ከመረብ ማገናኘት ሳይችል ቀርቷል።
በኤፍ ኤ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ ምሽት 1 ሰዓት ከ15 ቼልሲ ፖርትቬልን በሜዳው ሲያስተናግድ ምሽት 4 ሰዓት ላይ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ሳውዝሃምፕተንን ይገጥማል።

