Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ25ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ቀን 9 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች 0 ለ 0 ነው የተለያዩት።

በተመሳሳይ ስታዲየም አመሻሽ 12 ሰዓት መቐለ 70 እንደርታ ከሲዳማ ቡና ይጫወታል።

ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮጵያ ቡና ያገናኘው ጨዋታ ቀን 10 ሰዓት ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል።

በሊጉ ቀደም ብሎ ቀን 7 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 ማሸነፉ ይታወቃል።

Exit mobile version