Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

 አሜሪካ ጥቃት የደረሰበትን ኤፍ-15 ተዋጊ ጄት ፓይለት በህይወት አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ በኢራን ከተመታው የኤፍ-15 ተዋጊ ጄት ጥቃት በኋላ ጠፍቶ የነበረውን ፓይለት በህይወት ማግኘቷ ተሰምቷል።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናድ ትራምፕ ፓይለቱን ለማትረፍ የተደረገውን ዘመቻ በአሜሪካ ታሪክ ድፍረት እና ቆራጥነት የተሞላበት መሆኑን በመግለፅ፤ ዘመቻውን ላሳካው የነፍስ አድን ቡድን አድናቆታቸውን ችረዋል።

የኮሎኔል ማዕረግ እንዳለው የተገለፀው አብራሪው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በትሩዝ ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡

አብራሪው ለአንድ ቀን በኢራን ተራሮች ስር ተጥልሎ መቆየቱን ጠቅሰው÷ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠመውና በቶሎ እንደሚያገግም ገልጸዋል፡፡

የነፍስ አድን ዘመቻውን ለማሳካት በርካታ የጦር አውሮፕላኖች በስፍራው ተሰማርተው ለ24 ሰዓት ቅኝት ሲያደርጉ መቆየታቸቸውን መጠቆማቸውን ዘ ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡

ባለፈው አርብ ኢራን ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የአሜሪካ ኤፍ -15 ተዋጊ ጄት መትታ የጣለች ሲሆን ጥቃቱን ተከትሎ አንደኛው አብራሪ በህይወት ሲተርፍ ሁለተኛው አብራሪ ጠፍቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version