Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያን መውደድ የሚገለጠው የተሻለች ሀገር እንድትሆን በመስራት ነው – ደስታ ሄሊሶ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያን መውደድ የሚገለጠው የተሻለች ሀገር እንድትሆን በመስራት ነው አሉ የሥነ መለኮት አጥኚና መምህር ደስታ ሄሊሶ (ዶ/ር)።

ዜጎች ከድህነት እንዲወጡ፣ ስደተኝነት እንዲቆም፣ ሞራላዊ ልዕልና በኢትዮጵያ እንዲሰፍን እንዲሁም የበለጸገች ሀገር እንድትሆን በፍጹም ታማኝነት ማገልገል የሀገር ፍቅር መገለጫ ነው ብለዋል።

የሀገር ፍቅር ስሜት ከቃላት ባሻገር በሥራ ሊገለጥ እንደሚገባ ገልጸው፥ ኢትዮጵያ በታሪክ የነበራትን ታላቅነት ለመመለስና ሰላምን ለማረጋገጥ በአንድነት መስራት ይጠበቅብናል ነው ያሉት።

ሰላምን በዘላቂነት ለማጽናት ዋናው መንገድ ይቅርታ ነው ያሉ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት፣ የተከበረችና ተደማጭነቷ ከፍ ያለ ታላቅ ሀገር እንድትሆን ለይቅርታ ትልቅ ቦታ መስጠት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በብርሃኑ አበራ

Exit mobile version