Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

39 አባል ሀገራት የሚሳተፉበት የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባዔ ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 39 አባል ሀገራት እና ሌሎች ባለድርሻዎች የሚሳተፉበት የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም (ARC-COP 16) ጉባዔ ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጉባኤው በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ገልጿል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማሪያም (ዶ/ር) ጉባኤውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ ድጋፍ ራሷን ለመቻል የምታደርገው ጥረትና የመጣው ውጤት በመድረኩ በተሞክሮነት ይቀርባል።

የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን ለመፍታት ከሚሰራባቸው መስኮች መካከል በሰብዓዊ ድጋፍ ራስን መቻል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው÷ በመድረኩ መግባባት ለመፍጠር ምክክር ይደረጋልም ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያከናወች ስራ እና ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለማሟላት የተገበረቻቸው ተግባራት ለጉባዔው አስተናጋጅነት ተመራጭ እንዳደረጋት አንስተዋል፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ በአዲስ አበባ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ በማድረግ ኢትዮጵያን የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

በሰለሞን ይታየው

Exit mobile version