አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም አህጉራዊ የፋይናንስ ዘዴ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ አብሮነት ምልክት ነው አሉ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሺፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)፡፡
16ኛው የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባኤ ለአንድነት፣ ለአብሮነት እና ለሉዓላዊነት መሰለፍ በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ኮሚሽነሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በአህጉራችን የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ አደጋዎች መጠናቸው፣ ስፋታቸውና ውስብስብነታቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡
ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አብሮነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን ጠቅሰው፥ የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም አይነት ተቋማት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
በለይኩን ዓለም

