አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የስቅለትበዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በጸሎት፣ በስግደት እና በዝማሬ እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌልን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮቾች በተገኙበት በአዲስ አበባ ልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ነው እየተከናወነ የሚገኘው።
ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከጎኑ የተሰቀለውን ወንበዴ ይቅር ብሎ ለመንግሥተ ሰማያት እንዳበቃው ህዝበ ክርስቲያኑ ይቅር በመባባል ዕለቱን ሊያስበው ይገባል ብለዋል።
የስቅለት ቀን ምዕመኑ ንስሃ በመግባት ከጌታው እርቅ የሚያገኝበት ትልቅ ዕለት እንደሆነም አስረድተዋል።
በዚህ ዕለት ቀኑን የሚያወሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እየተነበቡ ሲሆን በዕለተ ስቅለት የተከናወኑ ተግባራትም በስግደት እየታሰቡ ይገኛል።
በቅድስት ብርሃኑ

