Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለ897 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ897 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የሕግ ታራሚዎቹ በይቅርታ ከእስር እንዲፈቱ የወሰኑት የክልሉ የይቅርታ ቦርድ የቀረቡለትን ጥያቄዎች በአዋጅና በመመሪያ መሠረት በጥልቀት መርምሮ ካጸደቀ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም መሠረት 875 ወንዶች እና 22 ሴቶች በድምሩ 897 የሕግ ታራሚዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
የይቅርታ ቦርዱ ውሳኔውን ያሳለፈው የታራሚዎቹን መታረምና መልካም ስነ ምግባር፣ እንዲሁም የወል ጥቅምን ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
ይቅርታው የተሰጠው ታራሚዎቹ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ተገቢውን የለውጥና የእርምት ስልጠና ወስደው ለማህበረሰቡ የማያሰጉ ዜጎች መሆናቸው ታምኖበት መሆኑን የገለጹት ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ ታራሚዎቹ በቀጣይ የሰላም ሰባኪ፣ አምራችና ህግ አክባሪ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ህብረተሰቡ የተፈቱትን ወገኖች የእርምት ሂደታቸውን አውቆ በክብር እንዲቀበላቸውም ጥሪ አቅርበዋል።
Exit mobile version