አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መላው ዓለም በከፍተኛ ትኩረት ይጠብቀው የነበረው የአሜሪካና ኢራን የሰላም ድርድር ያለ ስምምነት ተቋጭቷል።
ድርድሩ ያለስኬት መጠናቀቁን የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ይፋ አድርገዋል።
እንደ ፎክስ ኒውስ ዘገባ ኢራን የአሜሪካንን የድርድር ነጥቦች አለመቀበሏ ተጠቅሷል።
ዓለም በጉጉት ይጠብቀው የነበረው የሀገራቱ ውይይት በፓኪስታን አሸማጋይነት ኢስላማባድ የተካሄደ ነበር።

