Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት የምገባ መርሐ ግብር አከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ለአቅመ ደካማ የማሕበረሰብ ክፍሎች ማዕድ በማጋራት የትንሳኤን በዓልን በጋራ አክብረዋል።

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ በዓሉን ስናከብር መሰል ተቋማትን ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር በመገንባት ለዜጎች ያለንን ፍቅር በመግለፅ ማህበራዊ እሴቶችን ማጠናከር ይገባል።

በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር ያለ ልዩነት ያሳየበት እንደመሆኑ ዕለቱን ተደጋግፎና ተረዳድቶ በማሳለፍ ለዓላማው መኖር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል ከንቲባዋ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሽሮሜዳ አካባቢ 27ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከልን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

የምገባ ማዕከላት መስፋፋት መንግስት የዜጎችን ማሕበራዊ ችግሮች ለመፍታት የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ እንደሆነም አስረድተዋል።

በጀማል አህመድ

Exit mobile version