Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሁሉም ነገር መሰረት የሆነውን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ሁሉም ኃላፊቱን ሊወጣ ይገባል – የሃይማኖት አባቶች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሁሉም ነገር መሰረት የሆነውን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ሁሉም ኃላፊቱን ሊወጣ ይገባል አሉ የሃይማኖት አባቶች፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት 7ኛዉ ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የሀይማት አባቶች በዚህ ወቅት ባስተላፉት መልዕክት፤ መቻቻል፣ መከባበር እና አብሮነት የኢትዮጵያውያን መገለጫ መሆኑን አንስተው ይህንን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡

ሁሉም የአባቶችን የሰላም ጥሪ መቀበል እንዳለበት ገልጸው፤ ሰላም ከመንግሥት ብቻ የሚጠበቅ ሳይሆን እያንዳንዳችን የምንገነባዉ ነዉ ሲሉም አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የግል አጀንዳ የሚያራምዱ አካላት መኖራቸውን ጠቅሰው፤ በሃይማኖት ካባ ዉስጥ ተሸሽገዉ የሀገርን ሕልውና የሚሸረሽሩትን ጥፋተኞች መንግሥት ተጠያቂ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

በአመለወርቅ መኳንንት

Exit mobile version