Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ የቀብር ሥነ ሥርዓት በነገው ዕለት ይፈጸማል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ የቀብር ሥነ ሥርዓት በነገው ዕለት ይፈጸማል።

የአምባሳደር ቆንጂት ቀብር ሥነ ሥርዓቱ ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በእንጦጦ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀው።

አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

አምባሳደሯ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በ1950ዎቹ በለጋ እድሜያቸው ተቀላቅለው ከዴስክ ኦፊሰርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት አገልግለዋል።

እንዲሁም በኦቶዋ፣ ካይሮ፣ ቴል አቪቭና ቬይና በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን÷ በአፍሪካ ሕብረትና በተባባሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ መልዕክተኛ በመሆንም ሰርተዋል።

ከሰኔ 2009 እስከ መስከረም 2011 ዓ.ም ደግሞ ኢጋድ በመራው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ላይ ልዩ አማካሪ ሆነው ማገልገላቸው ተመላክቷል።

Exit mobile version