Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሊቨርፑል እና አስቶን ቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ 

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ 33ኛ ሳምንት ጨዋታ ሊቨርፑል እና አስቶን ቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

በመርሲሳይድ ደርቢ ከኤቨርተን ጋር ጨዋታውን ያደረገው ሊቨርፑል 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ሞሀመድ ሳላህ እና ቨርጂል ቫንዳይክ ለሊቨርፑል እንዲሁም ቤቶ ለኤቨርተን ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡

በተመሳሳይ ጨዋታ በቪላ ፓርክ ሰንደርላንድን ያስተናገደው አስቶን ቪላ 4 ለ 3 አሸንፏል፡፡

ኦሌ ዋትኪንስ (ሁለት)፣ ሞርጋን ሮጀርስ እና ታሚ አብርሃም ለአስቶንቪላ እንዲሁም ክሪስ ሪግ፣ ትራይ ሀም እና ዊልሰን ኢስዶር የሰንደርላንድን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ ኖቲንግሃም ፎረስት ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘውን በርንሌይ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡

Exit mobile version